የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሀገር ኩራትና ለባንክ ስራ መሰረት የጣለ ባንክ መሆኑን ተገለፀ

Date:

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዳሽን ባንክ 30ኛ አመት የምስረታ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሲያስተላልፍ የዳሽን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው አለሙ እንዳሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሀገር ኩራት እና በኢትዮጵያ ላሉ ሁሉም ባንኮች ለባንክ ስራ መሰረት የጣለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዳሽን ባንክ ከምስረታው ጀምሮ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን አቶ አሰፋው ጠቁመው ወደፊትም በተለያዩ ጉዳዎች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ለዳሽን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚና ሌሎችም የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ያስተላለፈውን ልዑካን ቡድን የመሩት የባንካችን የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አልሰን አሰፋ ዳሽን ባንክ ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ስኬታማ ከሆኑ የግል ባንኮች መካከል አንዱ መሆኑን አስታውሰው በትብብር እና በጋራ በመስራት እንደሚታወቅና የአገር ኩራት የሆነ የግል ባንክ መሆኑን ገልፀዋል።

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ታህሳስ 22 ቀን 1988 ዓ.ም ፈቃድ አግኝቶ በይፋ ሥራ የጀመረው ዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ከጃንዋሪ 1 ቀን ጀምሮ ለሦስት ወራት እያከበረ ይገኛል።
(ኢንባ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...