የኢትዮጵያ ንግድ ፖሊሲ ከሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታውን ባገናዘበ መልኩ ለመስራት ያስችላል

Date:

የሀገራችን ንግድ ለ117 ዓመታት ያለፖሊሲ ሲሰራበት ቆይቶ አሁን ተዘጋጅቶች ለመጨረሻ አስተያየት የቀረበው የኢትዮጰያ ንግድ ፖሊሲ የሀገራችንን ሁኔታ ከውጪው ዓለም ጋር በማስገንዘብ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ፖሊሲው የተዘጋጀው በምሁራን ተሳትፎ የተካሄደ ጥናት እና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን መነሻ በማድረግ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ ጸድቆ ወደተግባር ሲገባ ለንግዱ ማህበረሰብ በጣም ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡
ሌሎች ሀገራት የኢትዮጵያን የንግድ ስርዓት በተመለከተ ለሚጠይቁት ጥያቄ መልስ የሚሰጥ እንዲሁም የኢትዮጵያን የንግድ መልከዓ ምድር የሚያሳይ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው የዓለም ንግድ ድርጀት የአባልነት ድርድር እና ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ ሀገራዊ ጠቅምን ያስከበረ ፋይዳ የኖረዋል በማለት አስገዝበዋል፡፡

ረቂቅ የንግድ ፖሊሲው በዛሬው እለት በተካሄደው ከባለድርሻ አካላት የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ በተገኙ ገንቢ አስተያየቶች ዳብሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሚመለከተው አካል ይቀርባልም ብለዋል፡፡

ምንጭ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒሰቴር

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ ከኢራን ጋር የተስማሙባቸውን ነጥቦች ከአርብ በፊት ይፋ ሊያደርጉ ይችላሉ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነቱን ለማቆም የተስማሙባቸውን...

‹‹ሃገረ ትግራይ›› በዘመናት መነፅር ሲታይ

(አጭርዳሰሳ) በወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ) የመጽሐፉርዕስ፡- ሃገረ ትግራይ የመጽሐፉ ዓይነት፡-...

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...