ፎርቹን ቁጠባና ብድር የምስረታ ጉባኤ ተካሄደ

Date:

ፎርቹን የቁጠባና ብድር ህ/ስራ ማህበር በዛሬዉ እለት ምስረታውን እንዲሁም የአባላት ምርጫ መርሀ-ግብር አከናዉኗል።

ፎርቹን የቁጠባ እና ብድር ማህበር በሀገራችን ውስጥ እየተሰጠ ያለውን የቁጠባና ብድር አገልግሎት በቴክኖሎጂ በማስደገፍና ምንም የፋይናንስ ተደራሽ ላልሆነው የህብረተሰብ ክፍል የቁጠባና ብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የተቋቋመ ማህበር ነዉ።

የፎርቹን የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር መስራች የሆኑት አቶ አሸናፊ ከበደ፥ ፎርቹን ከ981 በላይ አባላት እንዳሉት እና ተመራጭ የብድርና ቁጠባ ማህበር ለመሆን እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

እንዲሁም ይህ ማህበር ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ቴክኖሎጂና በዘርፉ ብቃት ያላቸውን የሰለጠኑ ባለሙያዎች በማካተት በ2030 በአፍሪካ ተመራጭና ቀዳሚ ማህበር ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግሯል።

በተጨማሪም ሙስሊም እህት ወንድሞች ከወለድ ነፃ የቁጠባና ብድር አገልግሎት በልዩነት መዘጋጀቱም ተገልጿል::

እንዲሁም አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ሳደቀሩ በየጊዜው ትንሽ ትንሽ ገንዘብ በመቆጠብ ድንገተኛ የገንዘብ ፍላጎታቸውን (ለምሳሌ የህክምና ወጪ) ለመሸፈን ይችላሉ።

በተጨማሪም አነስተኛ ብድር በመዉሰድ የራሳቸውን አነስተኛ ንግድ በመጀመር ከድህነት ሊወጡ እንደሚያስችል እንዲሁም በዛሬዉ እለት የአመራር እንዲሁም የኮሚቴ ምርጫ መረጣ መርሀ-ግብር ተካሂዶ በአባላቱ ፀድቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...