ትራምፕ እንደተናገሩት ማዱሮ ከታሰሩ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ ቬንዙዌላን የማስተዳደር ፍላጎት እንዳላት እና የአሜሪካ ነጋዴዎች የነዳጅ መሰረተ ልማቱን ለመጠገን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቬንዙዌላዋ ምክትል ፕሬዝዳንት ዴልሲ ሮድሪጌዝ ዩናይትድ ስቴትስን እንዳትገዳደር አስጠንቅቀዋል።
”ትክክለኛውን ነገር ካላደረገች በጣም ከፍተኛ ዋጋ ትከፍላለች፣ ምናልባትም ከማዱሮ የበለጠ” ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ለ’ዘ አትላንቲክ’ መጽሔት በስልክ ቃለ መጠይቅ ተናግረዋል።
ትራምፕ ሮድሪጌዝ “እኛ አስፈላጊ ነው ብለን የምናስበውን ለማድረግ ዝግጁ ነበረች” እናም ሀገሪቱን የማስተዳደር ኃላፊነት ተረክባለች ብለው ነበር፤ እሷም ከጥቂት ቆይታ በኋላ በሰጠችው ምላሽ ለእሷ ማዱሮ አሁንም ፕሬዝዳንት መሆኑን ገልጻ እንዲፈታም ጠይቃለች።
