ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡርን ጎበኙ

Date:

“ዛሬ ወደ የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አ.ማ ጉብኝት አድርገናል። ጉብኝቱ የሀገራችንን ብሔራዊ የሎጂስቲክስ ክዋኔ ዐቅም ለመገምገም እና የሀገሪቱን እያደገ ያለ የልማት አጀንዳ ለመደገፍ በሎጂስቲክስ ዝግጁነት ላይ ገንቢ ውይይቶችን ለማካሄድ ጠቃሚ ዕድል ሰጥቶናል።


ኢኮኖሚያችን እያደገ ሲሄድ የሎጂስቲክስ ዘርፉ ካልዘመነ ዘላቂ ዕድገትን የሚገድብ ዋና መሰናክል መሆኑን ይቀጥላል። አሁን በተለይ በውስጣዊ እና በራስ ዐቅም የባቡር መንገድ ግንባታ ላይ የተመዘገበው ዕድገት እጅግ የሚያስደንቅ ነው።

ይህም የሀገር ውስጥ ዐቅምን ለመገንባት፣ ውጤታማነትን ለማሻሻል እና በባቡር ዘርፍ ውስጥ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ያለንን ጽኑ ቁርጠኝነት ያሳያል።

ሎጂስቲክስ ከባሕር እስከ መጋዘኖች ድረስ ያለውን ሙሉ ሰንሰለት ያካትታል። ይህም ወደቦች፣ የባቡር መንገዶች፣ አውራ ጎዳናዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶች እና የማከማቻ ተቋማትን ይጨምራል።

በአሁኑ ወቅትም በእጃችን ውስጥ ባሉ መስኮች ላይ እንደ ደረቅ ወደቦች፣ የባቡር መሠረተ ልማት፣ አውራ ጎዳናዎች እና የመጋዘን ግንባታ አስፈላጊ ማሻሻያዎችና ዘመናዊ የማድርግ ሥራዎች በሂደት ላይ ናቸው። እነዚህን ተያያዥ የሎጂስቲክስ ክፍተቶችን በተቀናጀ መንገድ መፍታት የዘርፉን መሰናክሎች ለመሻር እና የሀገሪቱን ሰፊ የልማት ግቦች ለመደገፍ ወሳኝ ይሆናል።” ብለዋል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...