በሳዑዲ አረቢያ የሙቀት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ፤ ሁጃጆች አረፋ ተራራ በሚያካሄዱት የሀጅ ስነ ስርዓት ድንኳን ውስጥ እንዲቆዩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
የሳዑዲ አረቢያ ሀጂና ኡምራ ሚኒስትር ተውፊቅ አል ረቢያ እንደገለጹት፥ ሁጃጆች በአረፋ ዕለት ከረፋዱ 4 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ባለው ጊዜ በአረፋ ተራራ ከፍተኛ ሙቀት የሚስተዋልበት በመሆኑ በድንኳናቸው ውስጥ እንዲቆዩ መጠየቃቸውን አል አረቢያ ኒውስ ዘግቧል።
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሁጃጆች አረፋ ተራራ ላይ የሀጅ ስነ ስርዓት ለማከናወን በስፍራው የሚገኙ ሲሆን፤ ከሙቀት ጋር በተያየዘ መጨናነቅና የጤና እክል ውስጥ እንዳይገቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
