ከምርት ወደ ወደብ እና ከወደብ ወደ ምርት ንግድን ላይ ስብሰባ ተካሄደ

Date:

የኢትዮጵያ ፍሬት ፎርዋርደርስ ኤንድ ሺፒንግ ኤጀንትስ አሶሴሽን ፣ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ እና ኩነ ፋውንዴሽን አንድ ላይ ያዘጋጁት ይህ ኮንፍረንስ የኢትዮጵያ የአቅርቦት ሰንሰለት ችግርን በስፋት የዳሰሰ ነዉ ተብሏል፡፡

“በማይበገር ሎጂስቲክስ አገልግሎትና የንግድ ማመቻቸት ሥራ ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባት” በሚል መሪ ቃል በተካደዉ ብሔራዊ የሎጂስቲክስ ኮንፈረንስ፤ በአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደርና በንግድ ማመቻቸት ሥራዎች ላይ ያሉ ስኬቶች፣እንቅፋቶችን እና መፍትሔያቸው ላይ ትኩረት ተደርጓል፡፡

“ከምርት ወደ ወደብ እና ከወደብ ወደ ምርት” ንግድን የማመቻቸት ሥራ በኢትዮጵያ፣ተግዳሮቶች፣ ዕድሎች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች” በሚሉ ርዕሶች ባለሙያዎችም ጥናት አቅርበዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የሎጅስቲክስ ዘርፍ ከዓለም ሁኔታ አንጻር ሲወዳደር እጅግ በጣም ዝቅተኛና ኋላቀር መሆኑም በስብሰባዉ ተነስቷል፡፡

በቂና ዘመናዊ የመሠረተ ልማት አውታሮች አለመኖራቸው፣ ለዘርፉ የሚመጥን የተቀናጀ፣ የተደራጀና የተናበበ ዘመናዊ የቴክኖሎጅ አጠቃቀም አለመኖሩ፣ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት፣ እና አገራችን የራሷ የባህር ወደብ የሌላት መሆኑ ለዚህ እንደ ምክንያት የሚጠቀሱ ጉዳዮች መሆናቸዉ ተገልጿል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...