በኢትዮጵያ ትልቁ ግብር ከፋይ እና የአርሶአደሮች አለኝታ ሃይኒከን ኢትዮጵያ አነስተኛ አቅም የነበራቸውን ሐረር እና በደሌ ቢራ ፋብሪካዎችን በመግዛት በኢትዮጵያ ሥራ የጀመረበት 15ኛ ዓመት ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም ቂሊንጦ በሚገኘው ፋብሪካው ደንበኞቹና አጋሮቹ በታደሙበት አከበረ።
በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ ትልቁን የቢራ ገበያ ድርሻ የያዘው ሃይኒከን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመርቶ ለገበያ ከቀረበ 157 ዓመታትን ያስቆጠረውን ዓለም አቀፍ ብራንዱን ሃይኒከን ቢራን ጨምሮ ሐረር፣ ፣ በደሌ ልዩ፣ በደሌ መደበኛ፣ ዋልያ፣ ዴስፔራዶስ የቢራ መጠጦች እንዲሁም ከአልኮል ነፃ የኾኑ ምርቶቹየ። “ሶፊ” እና “ቡክለር” ለገበያ በማቅረብ ይታወቃል።
ባርት ደ ኬኒንክ የሃይኒከን ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር በበዓሉ መክፈቻ መርሐግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ባለፉት 15 ዓመታት ኩባንያው ካከናወናቸው በርካታ ተግባራት መካከል የኢትዮጵያ የቢራ ገብስ ምርት የእሴት ሰንሰለት ልማት በትልቁ የሚጠቀስ ነው።
እ.ኤ.አ. በ2011 ከ2 ሺ 500 ገበሬዎች ጋር የተጀመረው ከ120 ሺ በላይ የኢትዮጵያ ገበሬዎች ጋር የተገናኘ የአቅርቦት መረብ መዘርጋት አስችሏል። እ.ኤ.አ. በ2023፣ ሃይንከን ኢትዮጵያ 100% የአካባቢ ገብስ ምንጭን በማስመዝገብ፣ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በኢትዮጵያ በሚመረት ገብስ በመተካት የገበሬዎችን ምርታማነት፣ የገቢ ዕድገት እና ኑሮ በመደገፍ ረገድ ተሳክቶለታል።
ኩባንያው ከ 103 ቢሊዮን ብር በላይ የግብር ግዴታውን በመወጣት ለተከታታይ 8 ዓመታት የከፍተኛ ግብር ከፋይ ሽልማትና ምሥጋና ተቋዳሽ ኾኗል።
📍ከቢራ ማምረትና መሸጥ ባሻገር:-
በኢትዮጵያ 15 ዓመታት (2011-2026) በቆየባቸው ዓመታት ከ1 ቢልየን ዩሮ በላይ መዋዕለንዋይ በኢትዮጵያ አፍስሷል፣
100% ለቢራ አስፈላጊ የኾነ የገብስ ምርት በሀገር ውስጥ አምራቾች እንዲተካ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል።
በገብስ እሴት ሰንሰለት ውስጥ ከ120 ሺ በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መኾን ችለዋል። በዚህም መሰረት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ማስቀረት ተችሏል።
ከ2 ሺ 500 በላይ ሠራተኞችን በማቀፍ በየዓመቱ 400 የአገር ውስጥ አቅራቢዎች ሥራ ላይ ማሰማራት ችሏል።
በአጠቃላይ በእሴት ሰንሰለቱ ውስጥ 137 ሺህ ሰዎችን በማሳተፍ ሥራ መፍጠር ችሏል።
ከ82 ሺ 800 በላይ የማህበረሰብ አባላት ደግፏል። ከጨ4 ሺ በላይ ሰዎች በደራሽ መጠለያ ፕሮጀክት ተጠቃሚ በማድረግ ጥቂት የማይባሉ ወገኖችን አአስከፊ የጉስቁልና ሕይወት ታድጓል።
ከሠራተኞቹና ከአጋሮቹ ጋር በመኾን ከ7 ሺ 400 በላይ ሄክታር መሬት በማልማት 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዛፎች በመትከልና በመንከባከብ ውጤታማ ኾኗል።
ሃይኒከን ኢትዮጵያ ላለፉት 15 ዓመታት አብረውት ለነበሩና በኩባንያው ዕድገት አሻራቸውን ላሳረፉ ደንበኞቹና አጋሮቹ የእውቅና የምስክር ወረቀት በመስጠት አመስግኗል።
