አርቲስት አብርሃም ቀናው ራሱ የሚተውንበት «አትጥሪኝ» የተሰኘ አዲስ የቴአትር ተውኔት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም ረቡዕ ከቀኑ 11:30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በልዩ ሁኔታ ለተመልካች እንደሚቀርብ ተገለጸ።
ይህ የቴአትር መድረክ አርቲስቱን ለማገዝና አብሮነታቸውን ለማሳየት ለሚፈልጉ አድናቂዎቹና ጥበብ ወዳዶች የተዘጋጀ ሲሆን፤ የመደበኛ መግቢያ ዋጋው 200 (ሁለት መቶ) ብር መሆኑ ታውቋል።
በተጨማሪም የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ባስተላለፉት ጥሪ፤ የቪ.አይ.ፒ (VIP) መግቢያ ለማግኘት የሚፈልጉ ተመልካቾች አርቲስት አብርሃም ቀናውን ለማገዝ የቻሉትን ያህል የገንዘብ መጠን «1000308114671» በተባለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ሂሳብ ቁጥሩ ገቢ በማድረግ እና የከፈሉበትን ደረሰኝ በማሳየት የቴአትሩ ታዳሚ መሆን እንደሚችሉ አስታውቀዋል።
ታዳሚያዎች ገንዘብ በሚያስተላልፉበት ወቅት በምክንያት (Reason) ቦታ ላይ «አትጥሪኝ ቴአትር» የሚል እንዲጽፉ ተመላክቷል።ስለ ዝግጅቱ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትም በስልክ ቁጥር 0901103400 ደውሎ መጠየቅ እንደሚቻል ተገልጿል።
