ሕገመንግሥታዊ ተቃርኖዎች፤ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት የማሻሻያ ሐሳቦችና ምክንያታቸው
በሚል ርዕስ በ🔹አቶ ፍሬሕይወት ሳሙኤል🔹 የተፃፈ በዓይነቱና በአቀራረቡ ለየት ያለና ስለኢትዮጵያ ሕገመንግሥት የማሻሸያ ሀሳቦች የሚዘረዝር መጽሓፍ
የካቲት 10/2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ግቢ እሸቱ ጮሌ አዳራሽ ታዋቂ ግለሰቦች፤ ምሁራንና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ይመረቃል።
አንቀፅ 39፤ ሰንደቅ ዓላማ፤ የአዲስ አበባ ሕዝብ መብት፤ የመሬት ባለቤትነት፤ የክልሎች አወቃቀር፤ ከፕሬዚዳንታዊና ከፓርላሜንታዊ የቱ ይሻላል?. . .ወዘተ በመፅሐፉ ውስጥ በዝርዝር ተዳሰዋል።
ስለሆነም መጥተው እንዲሳተፉ በክብር ተጋብዘዋል።
አክባሪዎ
ፍሬሕይወት ሳሙኤል
