ማዕከላዊ ባንክ ባንኮች የማገገሚያ እቅድ እንዲያዘጋጁ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ አወጣ

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ከባድ የገንዘብ ችግር ሲያጋጥማቸው ራሳቸውን እንዲያገግሙ የሚያስችል ዝርዝር እቅድ እንዲያዘጋጁ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ ቁጥር SBB/93/2025 አውጥቷል። ይህ መመሪያ የባንኮችን የገንዘብ መረጋጋት ለማረጋገጥ እና ቀውስ ከመከሰቱ በፊት ዝግጁ እንዲሆኑ ለመርዳት ያለመ ነው።

በአዲሱ መመሪያ መሰረት፣ ሁሉም በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ባንኮች አጠቃላይ እና አስተማማኝ የማገገሚያ እቅድ ማዘጋጀት አለባቸው። ይህ እቅድ አስፈጻሚ ማጠቃለያ፣ ስትራቴጂካዊና የአመራር ትንተና፣ የማገገሚያ አማራጮችን፣ የአሰራር የአደጋ ጊዜ እቅድ እንዲሁም የግንኙነትና ይፋ የማድረግ እቅድን ማካተት ይኖርበታል።

የብሔራዊ ባንክ ዋና ዓላማ ባንኮች የገንዘብ ቀውስ ሲገጥማቸው ከብሔራዊ ባንክ ወይም ከመንግስት ልዩ ድጋፍ ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው የማገገም አቅም እንዲኖራቸው ማስቻል መሆኑን ገልጿል።

ካፒታል ከመመሪያው እንደተመለከተው ፣ ባንኮች በቂ እና የተለያዩ የማገገሚያ አማራጮችን ማካተት አለባቸው። እነዚህ አማራጮች የካፒታል እና  ስጋትን መቀነስ፣ በቂና የተለያየ የገንዘብ ምንጮችን ማግኘት፣ እንዲሁም እዳዎችን እንደገና ማዋቀርን የመሳሰሉ እርምጃዎችን ያካትታሉ።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...