“ሩሲያ የአሜሪካ ትልቅ ተስፋ ናት”ካርልሰን

Date:


  ሩሲያ ለአሜሪካ ትልቅ አጋር ልትሆን ትችላለች ሲል ታዋቂው ጋዜጠኛ  ታከር ካልሰን ተናገረ።

ሩሲያ ካላት የቆዳ ስፋት እና ተፈጥሮ ሀብት አንፃር ለዋሽንግተን ከማንም የተሻለች ናት ብሏል ካርልሰን።

የተሻለውን ከመመኘት  እና ለአሜሪካ ትቅደም  መርህ ፣ሩሲያ እጅግ ጠቃሚ እና አስፈላጊ ሀገር ናት ሲል በራሱ የዩቱዩብ ቻናል ላይ ተናግሯል።

ሞስኮ ትልቅ የቆዳ ስፋት ያላት ፣ የብዙ ማዕድን ባለቤት  እና የሀይል ክምችት የተጎናፀፈች በመሆኗ ለአሜሪካ አጋዥ መሆን ትችላለች ሲል ገልጿል።

በመከራ ጊዜ የሚረዳህ ከፈለክ ብቸኛዋ አማራጭ ሞስኮ ብቻ ከፊት የምትሰለፍ ሀገርም ናት ብሏል    ።

የአሜሪካ እና ሩሲያ  ግንኙነት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ  ባይደን በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረ ቢሆንም፣ የትራምፕ ዳግም ወደ ስልጣን መምጣት የሀገራቱ ግንኙነት እንዲሻሻል ሆኗል  የሚሉ በርካቶች ናቸው።

ይህ የካርልሰን አባባል ሞስኮ እና ዋሽንግተን ለወደፊት አንድ ታላቅ ነገር እንዳላቸው አመላካች እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች የጋዜጠኛው ሀሳብ ፖለቲካዊ ትርጉሙ ቀላል አይደለም ይላሉ። አርቲ ኒውስ  እንደዘገበው ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ለተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ወንድማማቾች

የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ተጫዋቾችን...

ኢንፊኒቲ ለቤትና ለመኪና መግዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ...

የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት...

ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ...