ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኪሳራው በ53 በመቶ እንደቀነሰለት አስታወቀ

Date:

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከሚያዚያ 2017 ዓ.ም እስከ መስከረም ወር 2018 ዓ.ም ማብቂያ ድረስ በነበረው የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱ ኪሳራው በ52.83 በመቶ እንደቀነሰ አስታወቀ። ይህም በኩባንያው ሥራ ላይ አዎንታዊ ለውጥ መጀመሩን የሚያሳይ መሆኑን ገልጧል።

ኩባንያው ኪሳራው እንዲቀንስለት ያስቻለውም በውጭ ምንዛሬ ማሻሻያው እንዲሁም ትግራይ እና ኦሮሚያን ጨምሮ በክልሎች ባለው የጸጥታ ሁኔታ መረጋጋት የተነሳ እንደሆነ መግለጹን ዘ ኢስት አፍሪካን ጋዜጣ በድረ-ገጹ ላይ አስነብቧል።

በዚህም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ2025/2026 ግማሽ በጀት ዓመት ኪሳራውን ያለፈው ዓመት ከነበረበት 218.6 ሚሊዮን ዶላር ወደ 103.1 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ማድረግ መቻሉን አመልክቷል።

ይህም የኩባንያው ኪሳራ በ52.83 በመቶ መቀነሱን ያሳያል የተባለ ሲሆን፣ ኩባንያው በኢትዮጵያ ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተመዘገበ ታላቅ መሻሻል መሆኑ ተጠቁሟል። ይህ ለውጥ የተገኘውም በውጭ ምንዛሪ የአሠራር ሥርዓት ማሻሻያዎችና በትግራይ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልሎች ባለው የጸጥታ ሁኔታ መረጋጋት ምክንያት መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።

ኩባንያው የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት የሆነውን ኤም-ፔሳን (M-Pesa) ሳይጨምር ሁሉም ዋና ዋና ዘርፎች በስድስት ወራት ውስጥ አዎንታዊ ዕድገት ማስመዝገባቸውን ገልጿል።

የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ፒተር ንዴግዋ “የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት እና አስተማማኝ በሆነ የሥራ ሁኔታ የተነሳ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አበረታች ውጤት ማሳየቱን ቀጥሏል” ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም በኬንያና በኢትዮጵያ ዘላቂ ዕድገትን ለማስመዝገብ ለውጥ አምጪ ምርቶችን በማስተዋወቅ፣ የደንበኞችን አገልግሎት በማሻሻል እንዲሁም ስልታዊ አጋርነቶችን በማጠናከር ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ገልጸዋል።አስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...