ኤለን መስክ የ1 ትሪሊየን ዶላር ፓኬጅ ክፍያ በቴስላ ኩባንያ ባለድርሻዎች ጸደቀላቸው።
ኩባንያው ትናንት ባካሄደው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ፥ የመስክን ክፍያ በ75 በመቶ ድምጽ አጽድቆላቸዋል።
መስክ በቀጣይ አስር ዓመታት የቴስላን ገበያ ዋጋ ማሳደግ እንዲሁም ራሳቸውን ችለው የሚንቀሳቀሱ ሮቦት ተሽከርካሪዎችን ወደ ገበያ ማስገባትት ይጠበቅባቸዋል።
እነዚህ ስኬቶችም መስክን በመቶ ሚሊየን የሚቆጠሩ አዳዲስ አክሲዮኖችን ያስገኙላቸዋል።
መስክ የቦርዱን ውሳኔ ሲያደንቁ ከበርካታ የአሜሪካ ፍርድ ቤቶች እና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት በአንጻሩ ተቃውመውታል።
