በአንድ ወር ውስጥ ለ3 ሰዎች የሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ ህክምና መስጠቱን የአለርት ሆስፒታል አስታወቀ

Date:

የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከጀመራቸው የህክምና አገልግሎቶች መካከል የሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ ተጠቃሽ ነው።በሆስፒታሉ የአጥንት ቀዶህክምና ስፔሻሊስት እና የመገጣጠሚያ ቅየራ ሰብ ስፔሻሊስት ዶክተር እላዊ ተዋበ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም በሆስፒታሉ ይህ ህክምና ሳይሰጥ በመቆየቱ በርካታ ታካሚዎች አገልግሎቱን ማግኘት ሳይችሉ ቀርተዋል።

ሆስፒታሉ ከዚህ በፊት የግማሽ ዳሌ ቅየራ ህክምናን ሲሰጥ መቆየቱን የህክምና ባለሙያው ገልፀው በተለያየ የጤና እክሎች ዳሌያቸው የተጎዳ እና ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ ሁኔታ የሚያጋጥማቸው ሰዎች በመኖራቸው የሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ  ህክምናን ለመጀመሪያ ጊዜ መጀመሩን ተናግረዋል። ሆስፒታሉ አገልግሎት መስጠት በጀመረበት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለ3 ሰዎች ይህን ህክምና ሰጥቷል።

የዳሌ መገጣጠሚያ የዳሌ ማቀፍያና የዳሌ ራስ የሚባሉ ሁለት ክፍሎች እንዳሉት የገለፁት ዶክተር እላዊ  የዳሌ መገጣጠሚያ በተለያዩ የጤና እክሎች ሲጓዳና ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በሚሆንበት ወቅት የዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ ህክምና ይሰጣል።የዳሌ መገጣጠሚያ ላይ ጉዳት ከሚያስከትሉ ምክንያቶች መካከል  የመገጣጠሚያ ብግነት፣የዳሌ ራስ መበስበስ፣ስብራትና ዉልቃት እንዲሁም ኢንፌክሽን ተጠቃሾች ናቸው።በአብዛኛው እንዲህ ያለው የጤና እክል ከእድሜ መግፋት ጋር በተያያዘ ይከሰታል ያሉት የህክምና ባለሙያው  ከመኪና አደጋዎች እና ከመገጣጠሚያ አካላት ስብራት ጋር በተገናኘ በወጣቶች ላይ ሊከሰት እንደሚችል አስረድተዋል።

የዳሌ ማቀፊያውና ራሱ በአንድ ላይ በሰዉ ሰራሽ አካል በሚቀየሩበት ጊዜ የሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ የሚባል ሲሆን ከቀዶ ህክምና በኃላ ታካሚዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንቅስቃሴ ለመጀመር እንደሚያስችላቸው የህክምና ባለሙያዎች ይገልፃሉ።ለጡንቻ ጥንካሬ የሚረዱ ስፓርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ፣ ጤናማ የአመጋገብ ስርአትን መከተል፣ አላስፈላጊ የሰውነት ክብደትን መቆጣጠር፣የጉልበትና የዳሌ ጡንቻዎችን ለማዳበር እንደሚያግዙ የህክምና ባለሙያው ምክራቸውን ለግሰዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...