በአዋሽ ባንክ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት የ1 ትሪሊየን ብር ክፍያ ተከናወነ

Date:

ባለፉት 6 ወራት በአዋሽ ባንክ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት የተከናወነው የክፍያ መጠን አንድ ትሪሊየን ብር ደረሰ።

ባንኩ “ለላቀ የደንበኞች እርካታ እንተጋለን” በሚል መሪ ሐሳብ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የደንበኞች ሳምንት ያካሂዳል።

የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፀሐይ ሽፈራው ባንኩ ከደንበኞች ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 1 ሺህ ቅርንጫፎች እንዲሁም 24 ሰዓት አገልግሎት በሚሰጡ የዲጂታል ባንኪንግ ለደንበኞቹ አገልግሎቶች እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ባንኩ ስራ ፈጣሪዎችና አምራቾች ሀሳባቸውን ወደ ቢዝነስ እንዲቀይሩ በማስቻል ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገቡንም አውስተዋል።
የደንበኞች ሳምንት መርሐ ግብሩ ደንበኞችን ለማመስገን እና እውቅና ለመስጠት፣ የባንኩን ሰራተኞች ለተሻለ ስራ ለማነሳሳት እንዲሁም የደንበኞችን አስተያየት በመቀበል ለበለጠ ለውጥ ለመስራት ያለመ ነው ተብሏል።

ደንበኞች በአቅራቢያቸው የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ቅርንጫፎችን እያስፋፋ እና የዲጂታል ባንኪንግ ስርዓትን በበለጠ ለማዘመን እየሰራ እንደሚገኝም ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...