በአዲስ አበባ ከተማ አንድ ኪሎ ኮረሪማ ከ2 ሺህ 600  እስከ 2 ሺህ  700መቶ  ብር እየተሸጠ ነው

Date:

በአዲስ አበባ በተለያዩ የንግድ መደብሮች ላይ ለምግብ ማጣፈጫ ጥቅም ላይ የሚዉለዉ ኮረሪማ ዋጋው በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ብስራት ሬዲዮ ባደረገው ቅኝት ማወቅ ችሏል፡፡

ነዋሪዎች ለጣቢያችን እንደገለፁት በተለይም ካለፉት አስራ አምስት ቀናት  ጀምሮ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ተናግረዋል፡፡

በደቡብ ምእራብ ኢትዮጰያ ህዝቦች ክልል ከፋ ዞን በ17 ወረዳዎች የኮረሪማ ምርት በዋናነት የሚመረት ሲሆን በተጨማሪም በቤንች ሸኮ፣ በምዕራብ ኦሞ እና በሸካ ዞኖች  በብዛት ይመረታል፡፡

ካፋ ዞን በብዛት የኮረሪማ ምርት የሚመርትበት ቢሆንም ከሰሞኑ በዞኑ ከ1ሺህ 500 መቶ እስከ 1ሺህ 700 እየተሸጠ መሆኑን እና ታይቶ የማይታወቅ ጭማሪ ማሳየቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ኮረሪማ ከተተከለ ከ3 እስከ 5 ዓመት ቆይቶ ምርት መስጠት የሚጀምር ሲሆን አርሶ አደሮች ምርት መስጠት ከጀመረ በኋላ ከ7 እስከ 10 ዓመታት በየአመቱ ከ1 ሄክታር በአማካይ ከ30 ኩንታል በላይ ምርት ሊያገኙ እንደሚችሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡

በአዲስ አበባ በተለይም ካለፉት አስራ አምስት ቀናት ወዲህ የኮረሪማ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ዋጋው የጨመረበትን ምክንያት ብስራት ሬዲዮ የሚመለከታቸውን አካል አናግሮ በቀጣይ  ምላሽ ይዞ ይመለሳል፡፡

ዳጉ_ጆርናል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...