“በአዲስ አበባ ከተማ የወንጀል ምጣኔ 43 በመቶ ቀንሷል” 

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ባለፉት 11 ወራት ባከናወናቸው ተግባራት ዙሪያ ከሀይማኖት አባቶች፣ ከአባ ገዳዎች፣ ከሀገረ ሽማግሌዎች እና ከከተማዋ ነዎሪዎች ጋር ትላንት ተወያይቷል፡፡

የቢሮ ኃላፊዋ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለጹት፣ በመዲናዋ የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንዲሳኩ ሰላምና ፀጥታዉን ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራዎች ተጠናክረዉ ሲተገበሩ መቆየታቸዉን አንስተዋል፡፡

በተለይም በመዲናዋ ይከሰቱ የነበሩ ወንጀሎችን ለመቀነስ ህብረተሰቡን ባሳተፈ የተጠያቂነት አሰራ መዘረጋት በመቻሉ፣ የወንጀል ምጣኔዉ  ከአምናዉ ጋር ሲነፃፀር 43 በመቶ እንዲቀን ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

በከተማዋ ሰላም መረጋገጥ ላይ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በቅርበት እየሰራ የሚገኘዉ የሰላም ሰራዊትን አቅም ለማጎልበት የሚያስችል በሶስት ዙር ከ32 ሺ በላይ አዳዲስ የሰላም ሰራዊት አባላት እንዲቀላቀሉ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

መዲናዋ የጀመረቸዉ የ7/24 የልማት ትጋት እንዲሳካ፣ ህዝቡን የሰላም ባለቤት የማድረጉና ቅንጅታዊ ስራዎች ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉም ተመላክቷል፡፡

በተለይም በከተማዋ አይነታቸውን እና ቅረፃቸዉን እየቀያየሩ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን እና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ህዝብን የሚያማርሩ አካላት  በህግ እንዲጠየቁ የማድረጉ ስራ ትክሩት የሚሻ ነዉ ተብሏል፡፡

በቀጣይም የጋራ ትስስርን በመፍጠር ከተማዋን ወደ ከፍታ ማማ ለማሻገር እና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በጋራ መስራት እንደሚገባም በዉይይቱ ተነስቷል፡፡ #AMN

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...