በናይጀሪያ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ700በላይ ሳይደርስ እንደማይቀር ባለስልጣናት አስታወቁ።
ባለፈው ሐሙስ ሞክዋ በተባለቸው ከተማ ብቻ ከ200 በላይ አስከሬን መገኘቱን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በማዕከላዊ የኒጀር ግዛት በጎርፉ አደጋ ሳቢያ ከ500 በላይ ሰዎች የገቡበት አለመታወቁን እና እስካሁን አለመገኘታቸውን ሙሳ ኪምቦኩ የተሰኙ የአካባቢው ባለስልጣን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
አሁን ላይ በህይወት የተረፉ ሰዎች የማፈላለግ ስራው ተጠናክሮ ቢቀጥልም ሰዎቹ በአራተኛ ቀናቸው በህይወት ይገኛሉ ብለው እንደማያምኑም ነው የተናገሩት።
በሀገሪቱ በ60 ዓመታት ውስጥ ታይቶ አይታወቅም የተባለው ይህ የጎርፍ አደጋ በአካባቢው እጅግ ከባድ ጉዳት ማድረሱን ዘገባው ጠቅሷል።
ከሚያዝያ እስከ ጥቅምት ድረስ በሚቆየው የናይጀሪያ ዝናባማ ወቅት የጎርፍ አደጋ የተለመደ ሲሆን፥ የዛሬ ሦስት ዓመትበጎርፍ አደጋ ሳቢያ ከ600 በላይ ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ሰዎች መፈናቀላቸውን ዘገባው አስታውሷል።
