በኦሮሚያ ክልል የ4.5 ሚሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

Date:

ፈያ ኢንተግሬትድ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን በኦሮሚያ ክልል የሚከሰቱ የበሽታ ወረርሽኞችን እና አጣዳፊ የምግብ እጥረት ችግሮችን ለመከላከል የሚያስችል የ4.5 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።

የድርጅቱ መስራች እና ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንበሱ ቶላ እንዳሉት ይህ ባለብዙ ዘርፍ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ፕሮጀክት በጤና፣ በሥርዓተ-ምግብ እና በንፁህ መጠጥ ውሃ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነው።ፕሮጀክቱ 4.5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በጀት የተመደበለት ሲሆን ለዚህም በአሜሪካ መንግሥት የሚደገፈው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ፈንድ (EHF) ድጋፍ አድርጓል።

የፕሮጀክቱ ዋና ግብ በኦሮሚያ ክልል 5 ዞኖች በተመረጡ 7 ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ 295 ሺህ ገደማ የሚሆኑ ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎችን፤ በችግር ምክንያት የሚከሰቱ የህመም እና የሞት መጠኖችን ፈጣን እና የተቀናጀ ምላሽ በመስጠት መቀነስ መሆኑን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡

ፈያ ኢንተግሬትድ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ከ24 ዓመታት በላይ ለተቸገሩ ወገኖች የደረሰ ሀገር በቀል የልማት ድርጅት ሲሆን፤ የዛሬውን ከ295 ሺህ በላይ ወገኖች ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ይፋ ያደረገው 17ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን እያደረገ ባለበት ወቅት ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...