ከየካቲት 28_መጋቢት 28 የመራጮች ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበር ይታወቃል።
በተለያዩ ጉዳዮች የባከነ ጊዜን ለማካካስ እስከ ሚያዝያ 14 ተራዝሞ መጠናቀቁን የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላት ወርቅ ኃይሉ አስታውቀዋል።
በዚህም እስከ ዛሬ ቦርዱ ባገኘው መረጃ ከ50 ሚሊዮን በላይ መራጮችን መመዝገባቸውን የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ተናግረዋል።
ከ50ሚሊዮን ተመዝጋቢዎች ውስጥከ 45ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ መራጮች በማንዋል ሲመዘገቡ፤5ሚሊዮን የሚሆኑት በዲጂታል መመዝገባቸውም ተጠቁሟል።
በ48 ዋና እና ንዑስ የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ የመራጮች ጣቢያዎች ውስጥ 195ሺህ 3መቶ 16 ስራቸውን በህጉ መሰረት ሲሰሩ ለቆዩ አስፈፃሚዎች ከተመደበላቸው 1ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞ እየከፈለ ነው ብለዋል ሰብሳቢዋ።
በምዝገባ ወቅትም የሲስተምና የሰላምና ፀጥታ ጨምሮ የታዩ የተለያዩ ተግዳሮት እንደነበሩ ሰብሰባቢዋ ከመግለፅ አልሸሸጉም።
በአንዳንድ የክልል ምርጫ ጣቢያ ቁሳቁስ ለማጓጓዝ የፀጥታው ሁኔታ ፣ የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋት እና በአስፈፃሚዎች ላይ የታየ የስነ-ምግባር ግድፈት ለአብነት ተጠቅሷል።
ቦርዱ የማንነትና የወሰን ጥያቄ የሚነሳባቸው አካባቢዎችን በተመለከተም ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር እየተወያየ መሆኑን አስታውቆ፤ ውጤቱንም ይፋ አደርጋለሁ ብሏል።
7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚደረግ ይታወቃል።
