በጉራጌ ዞን የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ንፁሃን ለሞት ተዳረጉ

Date:

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በአማራ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በተከሰቱ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መድረሳቸውን የሚገልጽ መግለጫ በማውጣት፣ መንግስት የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ግዴታውን እንዲወጣ አሳስቧል።

ጉባዔው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ምስራቅ ጉራጌ ዞን፣ መስቃን ወረዳ የመዋቅር ጥያቄን ተከትሎ መስከረም 17 እና 18 ቀን 2016 ዓ.ም. በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ፣ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት የኃይል እርምጃ የቡታጅራ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ንፁሃን ዜጎች ለሞት መዳረጋቸውን አረጋግጧል።

በዚህ ክስተት ንብረት ላይም ውድመት መድረሱን ጠቅሷል። ኢሰመጉ ዛሬ ባወጣዉ መግለጫዉ የክልሉ መንግስት ጥቃቱን የፈጸሙ የጸጥታ አካላት ለህግ እንዲቀርቡና ለተጎጂዎች ፍትህ እንዲረጋገጥ አሳስቧል።

በተመሳሳይ፣ ኢሰመጉ በአማራ ክልል ግጭቶች ምክንያት የሚፈጸሙ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዳሉ አመልክቷል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የህወሓት የቃላት ጦርነት ንሯል።ይዋጉ ይሆን?

ሶስቱም ኃይላት የጦር ኃይላቸዉን እያጠናከሩ፣ አዳዲስ ተዋጊ እየመለመሉ መሆናቸዉ...

የሐማስ ታጣቂዎች ከእስራኤል ጋር በመተባበር የተከሰሱ ሰባት ሰዎችን ገደሉ

ሰኞ እለት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ያለ ቪዲዮ እንደሚያሳየው...