በጋዛ የተፈጠረው የጤና ቀውስ ገና ለትውልድ ይቀጥላል

Date:

ጋዛ “ለሚመጡት ትውልዶች የሚቆይ የጤና “አደጋ” እያጋጠማት ነው ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አስጠንቅቀዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም እንደተናገሩት የጋዛ ሰርጥ ህዝብ ውስብስብ ፍላጎቶች ለመፍታት ከፍተኛ የሆነ የእርዳታ መጠን መጨመር ያስፈልጋል ብለዋል።

እ.ኤ.አ ኦክቶበር 10 ከሃማስ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ከጀመረ በኋላ እስራኤል ተጨማሪ የህክምና አቅርቦቶችን እና ሌሎች ዕርዳታዎችን ወደ ጋዛ እንዲሻገር ፈቅዳለች ነገር ግን ዶ/ር ቴድሮስ የግዛቱን የጤና አጠባበቅ ስርዓት መልሶ ለመገንባት ከሚያስፈልገው በታች ነው ብለዋል ።

የተደረሰው ስምምነት በዋይት ሀውስ የተገለጸው ባለ 20 ነጥብ የሰላም እቅድ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን ይህም ወደ ጋዛ የሚገባውን የእርዳታ መጠን መጨመር እና ከሁለቱም ወገኖች “ያለ ጣልቃ ገብነት” የሚከፋፈሉ አቅርቦቶች ናቸው ።

ዶ/ር ቴድሮስ እንደተናገሩት የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንደሚቀበሉት ነገር ግን እየተላከ እና ወደ ጋዛ እየገባ ያለው ዕርዳታ ከተጠበቀው ያነሰ ነው ብለዋል።

በመሬት ላይ ስላለው ሁኔታ ሲጠየቁ ጋዛውያን ረሃብን፣ አስደንጋጭ ጉዳቶችን፣ የጤና አጠባበቅ ስርዓት ወድቀት ፣ በውሃ እና የንፅህና መሠረተ ልማቶች ውድመት ምክንያት የበሽታ መከሰት እንዳጋጠማቸው ተናግረዋል።

ማክሰኞ የመንግስታቱ ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከጥቅምት 10 ጀምሮ ከ6,700 ቶን በላይ ምግብ የያዙ የጭነት መኪናዎች ወደ ጋዛ ገብተዋል ብሏል፣ ነገር ግን አሁንም በቀን ከ2,000 ቶን በላይ ለማስገባት ከተያዘው እቅድ በታች ነው።

በቀን ስድስት መቶ የእርዳታ መኪናዎች ወደ ጋዛ መድረስ አለባቸው ነገር ግን በአማካይ ከ 200 እስከ 300 መካከል እየገባ ይገኛል። ዶ/ር ቴድሮስ የእስራኤል ባለስልጣናት ዕርዳታው እንዲገባ አስቻይ ሁኔታ እንዲፈጥሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ታጣቂ ኃይሎች ብቻቸውን የሚፈጽሙት ሳይሆን በመንግሥት ውስጥ ያሉ ኃላፊዎችም ጭምር …

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ከምሥረታው አንስቶ ባለፉት 7...

ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተሰጠ የኀዘን መግለጫ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በአርሲ ዞን ጥቅምት 10 እና...

 የ2026 የባሎንዶር ሽልማት አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ!

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፓሪስ ውጪ በለንደን በተካሄደው ታላቅ የሽልማት...

አይበገሬው ፍቃዱ —-  ( ከጋዜጠኛ ሁሴን ከድር )

ትናንት ( ቅዳሜ ጥቅምት 14 2019 ዓ.ም ) የቀድሞ...