በፊንላንድ ባህረ ሰላጤ የሩሲያ የጦር መርከብ በዩክሬን ድሮን ተመታ

Date:

ረቡዕ ዕለት በፊንላንድ ባህረሰላጤ የሩሲያ የጦር መርከብ ጥቃት እንደደረሰበት የፊንላንድ ባለስልጣናት አረጋገጡ። ይሁን እንጂ ስለ ጥቃቱ የታወቀው መረጃ ውስን ነው።
የዩክሬን ደኅንነት አገልግሎት በባልቲክ ባህር ዳርቻ በሚገኘው የሩሲያ ኡስት-ሉጋ የነዳጅ መላኪያ ማዕከል ላይ ባካሄደው ሰፊ የድሮን ዘመቻ፣ ‘ናሮ-ፎሚንሲክ’ የተባለችውን መርከብ ዒላማ ማድረጉን አስታውቋል።
የዩክሬን ድሮኖች ለሲቪል መርከቦች ክፍት በሆነ የባልቲክ ባህር አካባቢ በሚገኝ መርከብ ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ የመጀመሪያው እንደሆነ ይታመናል። ይህ ክስተት ዩክሬን ጥቃቶቿ ልታሰፋ ትችል ይሆናል የሚል ግምት ፈጥሯል።
ፊንላንድ ከዩክሬን የቅርብ አውሮፓውያን አጋሮች አንዷ ነች። የአገሪቱ ባለስልጣናት ክስተቱን ሩሲያ እያካሄደች ያለችው መጠነ ሰፊ ጦርነት ቀጥተኛ ውጤት ሲሉ ገልጸውታል።
የፊንላንድ ጦር ስለ ክስተቱ የሰጠው ዝርዝር መረጃ ውስን ቢሆንም፣ ጥቃቱ የተፈጸመው ከፊንላንድ የባህር ዳርቻ በተወሰነ ርቀት ላይ በሚገኝ ጠባብ የባህር ክፍል እንደሆነ ይታመናል።
የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤሊና ቫልቶነን በባልቲክ ባህር ውስጥ ያለው ሁኔታ የተረጋጋ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እንዲሁም በባህር ትራንስፖርት ላይ ምንም ዓይነት ስጋት አለመኖሩን በጽኑ ገልጸዋል።
የዩክሬን ደኅንነት አገልግሎት የሩሲያዋን መርከብ ካሊብር እና ኦኒክስ የተባሉ ክሩዝ ሚሳኤሎችን የምትሸከም ‘ቡያን ኤም’ ዓይነት አነስተኛ የጦር መርከብ ስትል ገልጻታለች።
ባህረ ሰላጤውን የምትዋሰነው የኢስቶኒያ መከላከያ ሚኒስትር ማርቲን ሄረም በበኩላቸው፣ መርከቧ ረቡዕ ጠዋት መመታቷን ገልጸዋል።
“ከዚያ በኋላ ከመርከቡ ጭስ ሲወጣ እንደነበር እናውቃለን። መርከቧ ወደ ሴንት ፒትርስበርግ አቅጣጫ ተመልሳለች” ብለዋል።
በሩሲያ የባሕር ኃይል መርከብ ላይ የደረሰ ሞት ወይም የንብረት ውድመት መጠን እስካሁን ግልጽ አልተደረገም፤ ሞስኮም እንዲህ ዓይነት ዝርዝር መረጃዎችን የምትሰጠው አልፎ አልፎ ነው።

BBC እንደዘገበዉ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሞዛምቢክ አቻውን 1 ለ 0 አሸነፈ

በ2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አስር ሦስተኛ መርኃ ግብር...

ፍሬሕይወት ታምሩ የአፍሪካን የቴክኖሎጂ ገጽታ ከቀየሩ 100 ሴቶች አንዷ በመሆን ተመረጡ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞ ዋና ሥራ...

ማንችስተር ዩናይትድ በይፋ አሰልጣኝ ሾመ !

ማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖን በሀላፊነት መሾሙን ይፋ አድርጓል። አሰልጣኝ...

የፕሪሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ይፋ...