ፍሬሕይወት ታምሩ የአፍሪካን የቴክኖሎጂ ገጽታ ከቀየሩ 100 ሴቶች አንዷ በመሆን ተመረጡ

Date:

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ፤ በአፍሪካ የዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ትልቅ አሻራ ያሳረፉ 100 ሴቶች መካከል አንዷ በመሆን አህጉራዊ እውቅና አግኝተዋል።

«አፍሪካ ሃይፐርስኬለርስ» እና «ዘ ሊትልስቴፕስ ግሩፕ» በጋራ ባወጡት በዚህ ዝርዝር ውስጥ የተመረጡት፣ ኢትዮ ቴሌኮምን በብቃት በመምራት፣ ኔትወርክን በማስፋፋት እና «ቴሌብርን» በማስተዋወቅ ለሀገራችን የዲጂታል ሽግግር ትልቅ መሰረት በመጣላቸው ነው።

በዚህ አህጉራዊ ዝርዝር ውስጥ ከእሳቸው ጋር የአፍሪካን የቴክኖሎጂ ገጽታ እየቀየሩ ያሉ እንደ ናይጄሪያዋ የ«ማይንዋን» መስራች ፋንኬ ኦፔኬ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሴት መሪዎች ተካተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሞዛምቢክ አቻውን 1 ለ 0 አሸነፈ

በ2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አስር ሦስተኛ መርኃ ግብር...

ማንችስተር ዩናይትድ በይፋ አሰልጣኝ ሾመ !

ማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖን በሀላፊነት መሾሙን ይፋ አድርጓል። አሰልጣኝ...

የፕሪሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ይፋ...

በፊንላንድ ባህረ ሰላጤ የሩሲያ የጦር መርከብ በዩክሬን ድሮን ተመታ

ረቡዕ ዕለት በፊንላንድ ባህረሰላጤ የሩሲያ የጦር መርከብ ጥቃት እንደደረሰበት...