በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል ያለዉ ግጭት እንዳሳሰበው የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን ገለፀ

Date:


የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን  በኢትዮጵያ ፌደራላዊ  መንግሥት እና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል በቅርቡ እየጨመረ የመጣው ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ውጥረት ተባብሶ ሌላ ግጭት ይከሰታል የሚል  ስጋት እንዳለው  በመግለጽ ውጥረቱን በማርገብ በሰላም መፈታት እንዳለበት አሳሰበ።

ድርጅቱ በትናንትናው ዕለት ባወጣው  መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው ከሆነ ከአካባቢው እና ከዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የተገኙ ዘገባዎች በአዲስ አበባ እና በመቀሌ መካከል ያለው ግንኙነት በቅርብ ሳምንታት ውስጥ እየተበላሸ መምጣቱን ያሳያሉ።

ይህ ሁኔታም በኢትዮጵያ እና ሱዳን አቅራቢያ ባሉ የድንበር አካባቢዎች አዲስ የትጥቅ ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት መፍጠሩን ጠቁሟል።

የፕሪቶሪያው ስምምነት አስከፊውን ጦርነት በማቆም ብሔራዊ እርቅ እና  ዘላቂ ሰላምን እና እምነትንን  ለመገንባት መንገድ የከፈተ  ታሪካዊ እድል ነው ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በትግበራው ላይ የተፈጠሩ አለመግባባቶች በተለይም በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እና በህወሓት መካከል ያሉ ውጥረቶች እንዲያይሉ  በማድረግ እንዲሁም በመቀሌ እና በአዲስ አበባ መካከል እያደገ የመጣው አለመተማመን እስካሁን የተመዘገቡ አዎንታዊ እርምጃዎችን አደጋ ላይ እየጣለ መሆኑን አስታውቋል።

ለፖለቲካዊ አለመግባባቶች ወታደራዊ መፍትሔ ሊኖር እንደማይችል የጠቆመው ፋውንዴሽኑ፣ ወደ ግጭት መመለስ በከባድ ጥረት የተገኘውን ሰላም ወደኋላ የሚመልስ እና ሰብአዊ መከራን የሚያበዛ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

የሰላም ፋውንደሽኑ አክሎም የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት በከፍተኛ ሁኔታ ትዕግስታቸውን ሊያሳዩ ይገባል ያለ ሲሆን ውጥረቱን ከሚያባብሱ እርምጃዎች እንዲቆጠቡ እና የፕሪቶሪያን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ለመተግበር ዳግም ቁርጠኛነታቸውን ማሳየት አለባቸው ሲል ጥሪ አቅርቧል።

በተጨማሪም እ.አ.አ. በ2030 ዓለም አቀፍ የሰላም ተነሳሽነት መሰረት ሁለቱም ወገኖች የሕዝብን ደህንነት እና ጥቅምን ከማንኛውም ፖለቲካዊና ወታደራዊ ፍላጎት አስቀድመው በመስጠት ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊና አካታች በሆነ ውይይት ሊፈቱ እንደሚገባ እናምናለን ሲል አሳስቧል።

አዲስ ማለዳ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር በዓለም የምግብ ምርምር ድርጅት ሹመት ተሰጣቸው

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአግራ (AGRA) የቦርድ ሰብሳቢ...

አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በካናዳ ሀገር ሊሸለሙ ነው

የሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ መስራችና ሊቀመንበር አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በንግዱ...

በምክክሩ ወቅት በሀሳብ ልዩነት “አድማ የመቱ” ነበሩ

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በ22ኛው ቀን ውሎው በስልታዊ ቡድን ደረጃ...

የብሔራዊ ትያትር ሕንፃ ግራጫ ቀለም የጥበብ ማዕከል መገለጫ አይሆንም

ከሥር ከላይ በስተግራ የምታየው ፎቶ 1 የታሪካዊዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ...