🟠 ትብብርን ማጠናከር፡ ሩሲያ እና ቻይና በሁሉም ዘርፎች ትብብራቸውን ያሳድጋሉ፤ የውጭ ተግዳሮቶችንም በጋራ ይፈታሉ።
🟠 ታሪካዊ መተማመን፡ ሁለቱም አገራት የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ታሪክን እውነታዎች የመቀየር እና የማሳሳት የፈጠራ ትርክቶችን ይዋጋሉ።
🟠 የጋራ ድጋፍ፡ ሞስኮ እና ቤጂንግ ዋና ዋና ፍላጎቶቻቸውን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ድጋፍ ይሰጣሉ።
🟠 የአየር ጉዞ መስፋፋት፡ መንግሥታቱ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የአየር ጉዞ ምልልስ ለመጨመር ተስማምተዋል።
🟠 “አንድ ቻይና” መርህ፡ ሩሲያ ታይዋንን የቻይና የማትነጠል አካል እንደሆነች በመቀበል “አንድ ቻይና” መርህን መከተሏን አረጋግጣለች።
🟠 የደህንነት ድጋፍ፡ ቻይና የሞስኮን ደህንነትን፣ መረጋጋትን እና ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጥረቶችን ትደግፋለች።
🟠 የንግድ መሻሻል፡ የጋራ ንግድ ማዕቀፍን ለማሻሻል ስምምነት ተደርጓል።
🟠 ቴክኖሎጂና ፈጠራ፡ በሳይንሳዊ-ቴክኒካዊ ፈጠራ እንዲሁም በከፍተኛ ቴክኖሎጂዎች ላይ ያለውን ትብብርን ይበልጥ ማጠናከር።
🟠 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፡ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትን ለመከላከል በዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ተቋማት ውስጥ ያላቸውን ትብብርን መቀጠል።
🟠 ብሪክስና ሻንጋይ የትብብር ድርጅት (ኤስሲኦ) ትብብር፡ በብሪክስ በኤስሲኦ ማዕቀፎች ውስጥ ትብብርን ማጠናከር።
🟠 የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ጥምረት ፡ ለኤይአይ የባለሙያዎች ምክር ቤት ማቋቋም እና የዓለም የኤአይ ትብብር ድርጅትን ለመመሥረት ዝግጁ መሆን።
🟠 አርክቲክና ሕዋ፡ በአርክቲክ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን፣ የሕዋ እንቅስቃሴዎችን ይበልጥ ለማጠናከር፣ የጨረቃ ጣቢያ ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ እና የጨረቃ ፍለጋ ተልዕኮ ቅንጅትን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆን።
