የበጋሻው ንግግር እናትን የልጇ ሬሳ ላይ አስቀምጦ እንደ መደብደብ ነው -ግልጽ Genocide ነው

Date:

የበጋሻው ንግግር ዛሬ አሁን በጥፊ እንደተመቱት ያህል የሚሰማንን ካህን ጉንጭ ጩኸት እኩል የማይረሳና የሚያቃጭል ነው!!!

በእኔ እድሜ አካባቢ ያሉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ተከታዮች በጋሻው ደሳለኝ፣ ዘርፌ ከበደ፣ ትዝታው ሳሙኤል፣  አሰግድ ሣህሉ….. የሚባሉ ሰዎች በጣም ያውቃሉ፡፡ ትምህርትና ጽሑፋቸውን፤ ስብከትና ዝማሬያቸውን በሰንበት ትምህርት ቤት ተምረን፤ በሬዲዮ ካሴት አዳምጠን፤ በአውደ ምህረት ቤተክርስቲያን ቁጭ ብለን ሰምተን፤ በቪዲዮ ተቀርጸው በሲዲ ተመልከተን፤ በብሎግ ጽፈው ፕሪንት አድርገን አንብበን ነበር ያደግነው፡፡

እነዚህ ሰዎች ሁሉም በሚባል ደረጃ የእኛን የታዳጊነትና የወጣትነት ዘመናችንን መንገዱ ልክ፤ ሕይወቱም ቀና ተከተሉት ብለው ቃል የገቡልንን፤ እንድታመንና እስከሞት እንድንይዘው የነገሩንን እውነት ክደው በተጻራሪ መልኩ ቆመዋል፡፡

አሁን ካሉን፣ ከሰበኩን፣ ከጻፉልን፣ ከመከሩ፣ ካስተማሩን ተጻርረው መጥተዋል፡፡ ያሉንን መካዳቸው ይሁን፡፡ የነገሩን ሃሳብ መቀየራቸው፣ መተዋቸው ይሁን፤ ያልሞተ ሰው ሃሳብ ይቀይራል ብለን አለፍነው፡፡

ግን የበጋሻውን የሰሞኑን ንግግር ላልፈው አልቻልኩም፡፡ ደግሞ ሰሞኑን “የቀድመው ፍቅርህን ትተሃልና የምነቅፍብህ ነገር አለኝ” ራዕ 2፡4 መሰረት አድርጎ የሰበከውን አንድ ስብከቱን እየሰማሁ ነበር፡፡ በጋሻው ልጀነቴን ካሳመሩ እና በመልካም ጎዳና ከመራኝ የቀድሞ ሰባኪዎች አንዱ ስለነበር፡፡ ለዚያም ነበር ዛሬም ልሰማው የወደድኩት፡፡

በጋሻው ግን ፍጹም ተቀይሯል፡፡ እኔ እንጂ እሱ ጭልጥ ብሎ የለም፡፡ በቅርቡ ለሞቱ ኦርቶዶክሶች ስላቅና ቂሙን አውጥቶ በመላው ኦርቶዶክሶች ላይ ተሳልቋል፡፡ በአርሲና በሌላውም የሚገደሉ ኦርቶዶክሶች የግድያው ዋና ምክንያት ሲያስቀምጥ፡፡ ሱፉን ለብሶ በማላገጥ መልክ እንደሚያለቅስ ህጻን ልጅ እያላገጠ…

“ካሴቴ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን  ተቃጠለ…ዘመን ጠበቀ እግዚአብሔር…ጊዜ ጠበቀ ሻሸመኔን ለኮሳት…አሁን ያ ሁሉ ተረስቶ ተጠቃን… አንተ ምን አድርገህ ነው ባለማህተቦች የታረዱት? እንዴ አንተ ምን አድርገህ ነው? ቄሱ የታረደው አንተ ምን አድርገህ ነው? ቤተመቅደሱ በእሳት የተለኮሰው ወይ አንተ ወይ አባቶችህ ዱሮ ምን አድርገው ነው? ሁሌ ተበዳይ አድርጎ ራስን ማቅረብ ልክ አይደለም…” እያለ በስሜት የኦርቶዶክሶች ሞት፣ እንግልት፣ መከራና ስቃይ ልክነቱንና ተገቢነቱን ይሰብከል። እነሱም ቁጭ ብለው ከፈሰሰው ንጹሐን ደም ስላቅን ተካፈሉ…

ጥያቄ እነ ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ጳውሎስ፣ ቶማስ፣ ዮሐንስ…ሐዋርያት ቅዱሳን በአጠቃላይ ያንን መከራ የተቀበሉት ወይ እነሱ ወይ አባቶቻቸው ምን አድርገው ነው? እያለ ነው። እና እውነት ምን አድርገው ነው በጋሻው?

ምንድነው ክርስትና? ምንድነው ክርስቲያን? ምንድነው ወንጌል? መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ነው የሚያስተምረው? ምንድነው በክርስቶስ አንድነት?

አሁን በጋሻው አፍ ኖሮት፤ ህይወትስ ኖሮት የወንጌል ቃል ከዚህ በኋላ ይናገራል? መናገሩንስ ይናገራል፡፡ ሰሚዎቹ፣ አድማጮቹ፣ ምእመኖቹስ ዛሬም ሞትና ስደትን ግድያን ያዋድዳሉ? ደህና ናቸው?

የማቴዎስ ወንጌል ቁጥር 5:44-45 ላይ ያለውን “እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።” ብሎ ይሰብካል፡፡ በጋሻው ከዚህ በኋላ በክርስቶስ ክርስቲያን የተባላችሁ፣ ወንድሞቼ ብሎ ይሰብካል?

በዚህ ደረጃ ቂምና ጥላቻ እንዴት ይያዛል? ቂም ከተያያዘ እኮ ከአንዳንድ የቤተክሀነት ሰዎች እንጂ ከመላው ኦርቶዶክስ ምእመን ጋር አልነበረም፡፡ ከቤተክህነት ሰዎች ጋር በጥቅማጥቅም ተባላ፣ በካሴት ማሳተም፣ በአውደምህረት ልፊያና በጸጋ መቀናናት የተጣለው እዛ ከእነሱ እንጂ ከመላ ምእመኑ ነበር? ከዚሁ ምእመን በሚወጣ ገንዘብና ጥቅማጥቅም እርስ በእርስ ተፋጁ እንጂ ምእመኑ ምን አደረገ?

እንዴት የንጹሐንን ሞት በዚህ መልክ justify ይደረጋል?ይሄ እናትን የልጇ ሬሳ ላይ አስቀምጦ እንደ መደብደብ ነው።

ይሁን ዛሬ እንደምንም ብሎ ያልፋል፡፡ ነገስ ለዛሬ ገዳዮች? ነገስ ለዛሬ ባለጊዜዎች? ነገስ ምን አድርገህ ነው እያለ ሊቀጥል ነው? “ምን አድርገህ ነው?” የሚለው ጥያቄ ያለው አንድ ዘመን ብቻ ነው፡፡ ምን አድርገህ ነው ማለት እኔም ብገልህ፤ ብችል ባጠፋህ ልክ ነው ማለት ነው፡፡ ይሄ ለኦርቶዶሶች ግልጽ Genocide ነው።

የበጋሻው ንግግር ዛሬ አሁን በጥፊ እንደተመቱት ያህል የሚሰማንን ካህን ጉንጭ ጩኸት እኩል የማይረሳና የሚያቃጭል ነው!!!

እናም አንረሳውም!
(ቃልኪዳን ኃይሉ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...