የሰሜን ለንደኑ ቡድን አርሰናል በ መጪው የ ኢንተርናሽናል ብሬክ ወቅት ላይ የ ወሳኝ ተጫዋቻቸው ቡካዮ ሳካን ኮንትራት ለማራዘም እንደሚሰሩ ተነገረ።
መድፈኞቹ አርሰናሎች ባሳልፍነው የክረምቱ የዝውውር መስኮት ካሳለፋት ድንቅ የዝውውር ጊዜ ቡሀላ አሁን ላይ ትኩረት አድርገው በ ቡድኑ ውስጥ የሚገኙ የቁልፍ ተጫዋቾችን ኮንትራት ለማራዘም እየሰሩ እንደሆነ ተመልክቷል ።
ቡድኑ ቀድም ብሎ የሁለቱን የመሀል ተከላካዮች ዊሊያም ሳሊባን እና የ ጋብሬል ማጋሌስን ኮንትራት ማራዘም የቻሉ ሲሆን አሁን ደግሞ የ ቡድኑን የማጥቃት መሰረት የ ቡካዮ ሳካን ኮንትራት ለ ረዥም ጊዜያት ያህል በሚያቆይ ውል በ ኤሜሬትስ ለማቆየት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ የተነገረ ነዉ።
መጪዎቹ ቀናቶች ደግሞ በአርሰናል የስፖርቲንግ ዳይሬክተር አንድሬያ ቤርታ እና በ ቡካዮ ሳካ የወኪሎች ካምፕ በኩል ስምምነቶችን እንደሚፈጠሩ ከ ሀገረ እንግሊዝ የሚወጡ የመረጃ ምንጮች አትተዋል።
ቡካዮ ሳካ በመድፈኞቹ ቤት ደስተኛ እንደሆነ ሲነገር በ ሚኬል አርቴታ የ ቡድን ፕሮጀክት ላይም ትልቅ እምነት እንዳለው እየተነገረ ይገኛል። አርሰናሎች የ ሳካን ብቻ ሳይሆን የ ጁሪያን ቲንበርንም ኮንትራት ለማራዘም እንደተቃረቡ ተሰምቷል።
