“ባለቤቴ ዘረፈኝ! ጎዳና ልወጣ ነው ድረሱልኝ” አትሌት ገለቴ ቡርቃ

Date:

አትሌቷ በሩጫ ዘመኗ ያገኘችውን ሀብትና ንብረት ባለቤቷ መውሰዱን ገልጻ፣ “ጎዳና ልወጣ ነው መንግስት ይድረስልኝ” ብላለች።

መኖሪያ ቤት እና መንግስት በተለያየ ጊዜ የሸለማት 11 መሬቶች ውስጥ አስሩ ባለቤቷ መሸጡን እና አሁን ካለችበት ቤት ለማስወጣት በፍርድ ቤት ጉዳዩን እየጨረሰ ነው ብላለች።

ካሏት 5 መኪናዎች 4 መኪኖችን ባለቤቷ መሸጡንም ገልጻለች።

በአሁኑ ወቅት ልምምድ አቁማ በፍርሃት ለአንድ አመት ከቤት ሳትወጣ መቀመጧን ተናግራለች።

“ፍርድ ቤት ሁሉንም ነገር እኔ ላይ እየፈረደ ነው የእኔን ጉዳይ እየተመለከተ አይደለም” በማለት በገመዳ ሾው ላይ ቀርባ ተናግራለች።

መንግስትና ህዝብ ይድረስልኝ ስትልም ጠይቃለች።

(Source: Ethiopian Women in Sports)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...