ባለፉት 20 ዓመታት በሀገሪቱ የተመዘገቡት የፓተንት (የመብት) ብዛት 500 ብቻ ነዉ

Date:

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን እስከ 2015 ድረስ በዓመት በሁሉም መብቶች ጥቂት ምዝገባ ማከናወኑን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመስል እንደገለፁት፤ ተቋሙ በርካታ አመታት ማስቆጠሩን የገለፁ ሲሆን በእነዚህ አመታት ግን ስራዎች ቢያከናውንም በሚፈለገው ልክ እንዳልነበርም ጨምረው አስረድተዋል።

ተቋሙ ባለፉት 20 አመታት 500 ፓተንት መመዝገቡን ተናግረው፤ ይህን ለማሻሻል የምዝገባ ስርዓቱ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ገልፀዋል።

ይህም የተነሳው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከናወኑ የምርምር ውጤቶችን ከማሳተም ባሻገር ፓተንት እንዲወጣባቸው ስለማይደረግ መሆኑን ተጠቁመዋል ።

ለዚህ አፈፃፀም ዝቅተኛ የሆነበት ምክንያት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከናወኑ የምርምር ውጤቶችን ከማሳተም ባሻገር ፓተንት እንዲወጣባቸው ስለማይደረግ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያከናውኗቸውን የምርምር ስራዎች ከማሳተም ባሻገር ወደ ፓተንት እንዲያሻግሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ካፒታል ከኢዜአ ያገኘዉ መረጃ ያመለክታል ።

አሁን ግን በ2017 በጀት አመት ስድስት ወራት ሶስት ሺህ መብቶችን መመዝገቡን የገለፀው ባለስልጣኑ ለቅጅና ተዛማጅ መብቶች፣ ለፓተንቶች(የግልጋሎት ሞዴሎችን ጨምሮ)፣ ለኢንዱስትሪያዊ ንድፎች እና ለንግድ ምልክቶች የመብት ጥብቃ እያደረገ ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...