በሀገራችን የሚሰበሰበው የደም መጠን ከህዝቡ ቁጥር አንፃር አነስተኛ ነው ተባለ

Date:

የኢትዮጵያ የደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት በደም ፍላጎትና አቅርቦት መካከል ክፍተት መኖሩን ገልጹዋል፡፡

ይህን የአቅርቦት እና የፍላጎት አለመጣጣም ችግርን ለማስተካከል የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እና የእምነት ተቋማት ትልቅ ሚና እንዳላቸው የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ ተናግረዋል።

በቂ የደም አቅርቦት እንዲኖር እና የደም ህክምና የሚፈልጉ ታካሚዎችን ህይወት ለመታደግ አሁንም ጥረቶች እየተደረጉ እዳሉ የገለጹ አቶ ሃታሙ በፍላጎት እና አቅርቦት መካከል አሁንም ክፍተት መኖሩን አስታውቋል።

በ2017 በጀት አመት 8 ወር ፤ለመሰብሰብ ከታቀደው 3 መቶ 42ሺ ዮኒት ደም ውስጥ 2 መቶ 75ሺ 2 መቶ 86 ዮኒት ደም ማሰባሰብ መቻሉን አንስተዋል ፡፡ ይህም ከታቀደው 80 በመቶ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በኦርቶዶክስ እና በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የፆም ወቅት በመሆኑ የደም እጥረት እንዳይከሰት ስራዎች እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...