እ.አ.አ. በ2026 የሚጀምረው አጋርነት የስኬታማውን ውድድር ዓለም አቀፋዊ ስም የበለጠ ከፍ ያደርጋል እንዲሁም ለልጆች የሩጫ እድሎችን በእጅጉ ያሰፋል፡፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እ.አ.አ. ከ2026 ጀምሮ ከባንክ ኦፍ አሜሪካ ጋር አብረው ለመስራት የበርካታ ዓመታት የአጋርነት ስምምነት ማድጋቸውን ዛሬ አሳውቋል፡፡ አጋርነቱ ባንኩ በረዥም ርቀት ሩጫ ላይ የነበረውን ግዙፍ እንቅስቃሴ ከአፍሪካ እጅግ ተለዋዋጭ እና በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ የሩጫ ማህበረሰቦች ወደ አንዱ እንዲያሰፋ ያግዘዋል፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሶስት ትልልቅ የሩጫ ሁነቶች (events) ላይ በጋራ ይሰራሉ – የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ ፣ የልጆች ሩጫዎች እና ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ.።
ባንክ ኦፍ አሜሪካ እነዚህን ውድድሮች ተጠቅሞ የኢትዮጵያን ደማቅ የሩጫ ባህል እይታ ለማሳደግ እና በስፖርት፣ ቱሪዝም እና ንግድ አማካይነት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ ለማድረግ ተዘጋጅቷል፡፡
