ትራምፕ የኢራንን ሰማይ ተቆጣጥረናል አሉ

Date:

ዶናልድትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ “አሁን በኢራን የአየር ክልል ላይ ሙሉ ቁጥጥር አለን” አሉ።

“ኢራን ጥሩ የአየር ክልሏን መከታተያ እና ሌሎች የመከላከያ መሣሪያዎች እንዲሁም ብዙ ነገር ነበራት። ነገር ግን አሜሪካ ከተሰራው፣ ከተፀነሰው እና ከተመረተው ‘ዕቃ’ ጋር አይወዳደርም። ማንም ከአሜሪካ የተሻለ አድርጎ አይሰራም” ብለዋል።

አሜሪካ ለረዥም ዓመታት ለእስራኤል ወታደራዊ ድጋፍ እና መሣርያዎች ስትሰጥ የቆየች ቢሆንም ከአርብ ጥቃት ወዲህ ጀምሮ እስራኤል በኢራን ላይ በፈጸመችው ጥቃት ዩናይትድ ስቴትስ እጇ እንደሌለበት ስትገልጽ ቆይታለች።

ዶናልድ ትራምፕ አክለውም “ ‘ጠቅላይ መሪ’ እየተባሉ የሚጠሩት ግለሰብ የት እንደተደበቁ በትክክል እናውቃለን።

እሱ ቀላል ዒላማ ነው። ግን እዚያ መሆናቸው መልካም ነው።እሱን አናወጣውም (አንገድለውም!) ቢያንስ ለአሁን።

“ነገር ግን ሚሳኤሎች በሠላማዊ ዜጎች ወይም በአሜሪካ ወታደሮች ላይ እንዲተኩሱ አንፈልግም። ትዕግሥታችን እያለቀ ነው። በጉዳዩ ላይ ትኩረት ስለሰጣችሁን እናመሰግናለን!”

ትራምፕ በተከታታይ በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ ባጋሩት በዚህ ጽሑፍ ላይ “ያለምንም ማወላወል እጅ መስጠት!!” ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...