ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ታስተናግዳለችል

Date:

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽ ጋር በጋራ በመሆን የሚያዘጋጁት 2ተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ መሆኑ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች በዓለም አቀፍ ደረጃ በመሪነት አዎንታዊ አስተዋፅዖ እያደረገች እንደምትገኝ፤ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ በትናንትናው ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽ ጋር በጋራ በመሆን 2ኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ በመዲናችን አዲስ አበባ ለማካሔድ በዝግጅት ላይ መሆኑንም ገልጸዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ በአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ በኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳይ የሚያስከትለው ተጽእኖ ቀላል የሚባል እንዳልሆነም አንስተዋል።

“በተለይ በግብርና ዘርፉ እና በጤናው ዘርፍ ላይ እያስከተለ ያለው ችግርም ከፍተኛ ነው” ብለዋል።

ይህንን ችግር ለመፍታት የፍይናንስ እጥረት መኖሩን አንስተው፤ በዚህ ጉዳይ የሚካሄደው ጉባኤ ከፍተኛ  መፍትሔ አመላካች እንደሚሆን ጠቁመዋል።

የኤፌዲሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥንና የአካባቢ ጥቢቃን በተመለከተ ሀገራዊ ዕቅዶችን ለማሳካት በዓለም ዓቀፍ፣ በአህጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ደረጃ  ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አንስተዋል።

በቀጣይ በአፍሪካ ደረጃ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት፣ የፋይናንስ ችግሩንም ማሻሻል ይገባል ብለዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤው የሚካሔደው ከጳጉሜን 3 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም. መሆኑ ተገልጿል።

በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የሚመክር አህጉራዊ ጉባኤ እንዲካሄድ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ፤ የመጀመሪያው  የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ በ2015 በኬንያ አስተናጋጅነት መካሄዱ ይታወሳል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...