ለቢዝነስ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ አካታች የዲጂታል ክፍያዎችን ከሚያቀርበው አሪፍ ፔይ ጋር የተደረገው ስምምነት፣ የባንኩ ደንበኞች በካርድ ክፍያ ያለችግር እንዲገበያዩ፣ እንዲከፍሉ፣ ክፍያዎችንና ሽያጮችን እንዲከታተሉ በማድረግ ግብይቶችን እንዲያቀላጥፉ የሚያግዝ አሠራርን ለመተግበር የሚያግዝ መግባቢያ ነው ተብሏል።
ዓለም አቀፍ አሠራርን ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ መሆኑም የተገለፀ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የጥሬ ገንዘብ አጠቃቀምን ወደቀነሰ ዲጂታል ቴክኖሎጂ አሠራር እድገት ለምታደርገው ጉዞ አጋዥ እንደሚሆን ተመላክቷል፡፡
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከዓለም አቀፍ ክፍያ ድርጅቶች ጋር በመሆን በአጋርነት ለደንበኞቹ ደህንነቱ እና ደረጃውን የጠበቀ የፋይናንስ ሥርአት እንዲጠቀም የሚያስችለው እንደሚሆንም ተጠቁሟል፡፡
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ የ3 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድና የ5 ዓመት ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ሥራ ላይ ለማዋል ዝግቶች ማጠናቀቁ በፊርማ ሥነ-ሥርአቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡
