የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ለኢራን ብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ጸሐፊ ሞህሲን ራይዚ ደብዳቤ መላካቸውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አረጋገጡ።ዋል ስትሪት ጆርናል ያወጣውን ዘገባ ተከትሎ ከጄዲ ቫንስ ደብዳቤ እንደተላከላቸው ራይዚ ይፋ አድርገዋል። ደብዳቤው መላኩን ያረጋገጡት ትራምፕ ይዘቱም መድኃኒት እና የሕክምና አቅርቦት መሆኑን ገልጸዋል።
ደብዳቤው ከድርድር ጋር የተያያዘ ነው ቢባልም ትራምፕ እንዳሉት ግን የሕክምና ቁሳቁስ እና መድኃኒት መላክል ይመለከታል።
ራይዚ “የሕክምና መገልገያዎች ማቅረብ ይፈልጋሉ። ጄዲ ቫንስ ምን እንደማስብ ጠይቆኛል። ማድረግ ከፈለጋችሁ ትችላላችሁ ብዬዋለሁ። የታመሙ ሰዎችን ለመርዳት የሚውል ቁሳቁስ መቅረቡ መልካም ነው” ብለዋል።
ዋል ስትሪት ጆርናል ትናንት ረቡዕ ባወጣው ዘገባ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ጠቅሶ ቫንስ ደብዳቤ መላካቸውን አስነብቧል።
የደብዳቤው ዓላማ የሰላም ውይይት ማስቀጠል መሆኑም በዘገባው ተመልክቷል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤው መድረሱን በተመለከተ መረጃ አልሰጠም። ሆኖም ግን በያዝነው ሳምንት የቀጣናው ከፍተኛ አመራሮች እና ወታደራዊ ባለሥልጣኖች በብዛት ወደ ቴህራን እየተጓዙ ነው።
ትራምፕ ለአጋማሽ ዘመን ምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ኢራን ላይ አዲስ ጥቃት መሰንዘር ሊጀምሩ እንደሆነ ሲያስጠነቅቁ ተደምጠዋል።
