በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል፥ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስም ካላቸው እና አንጋፋ ከሆኑት የጋዜጠኝነት ባለሙያዎች አንዷ ለሆነችው መዓዛ ብሩ የምስጋና መርሃግብር አካሂዷል።
በኢትዮጵያ የግል የኤፍ ኤም (FM) ሬዲዮ ጣቢያዎች አነሳስና እድገት ውስጥ ቀዳሚውን ሚና ከተጫወቱት መካከል የምትጠቀሰው መዓዛ፥ ከባህል ማዕከሉ ሽልማትም ተበርክቶላታል።
በሸገር ኤፍ ኤም ስር በሚተላለፉ እንደ «የጨዋታ እንግዳ» እና «ሸገር ካፌ» የመሳሰሉ ታዋቂ እና ሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፉ የሬዲዮ ፕሮግራሞች አዘጋጅና አቅራቢ በመሆን ሰፊ ዕውቅና ያተረፈቸው ጋዜጠኛዋ ከሸገር FM ሰራተኞችም ስጦታ ተበርክቶላታል።
ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ “መርሃ ስፖርት” በተባለ ጋዜጣ ላይ የስፖርት ዘጋቢ በመሆን የሰራች ሲሆን በብሔራዊ ባንክ “ብሪቱ” የተባለውን የባንኩን ወርሃዊ መጽሔት በዋና አዘጋጅነት መምራቷ የሚታወስ ነው።
