ቦሳድ የተሰኘው በአጥንት እና አጥንት ጉዳቶች ላይ የሚሰራው የጥናት ቡድን ባደረገው ጥናት ከ40 እስከ 70 በመቶ የሚሆኑ የእጥንት ታካሚዎች በመጀመሪያ ወደ ባህላዊ ህክምና ሄደው ከዚያ ወደ ዘመናዊ ህክምና የመጡ ናቸው ብሏል።
በተጨማሪም 78 በመቶ የሚሆኑት የጎንሽ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጿል።
በሌላ በኩል ደግሞ 26 በመቶ የሚሆኑት ወደ ጤና ተቋማት መጥተው ተመልሰው ወደ ባህላዊ ህክምና ያቀኑ ናቸው ተብሏል።
ጥናቱ በተለይ ህጻናት ለአጥንት ጉዳቶች ተጋላጭ ሲሆኑ፥ በዚህም 78 በመቶ የሚሆኑት በትምህርት ቤት የሚጎዱ መሆናቸው ተገልጿል።
በተለይ ለባህላዊ ህክምና የሚሄዱ የማህበረሰብ ክፍሎች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው፣ በገጠር ያሉ፣ ዘመናዊ ትምህርት ያልተማሩ፣ ክፍት ስብራት ያላቸው እና ህጻናት እንደሆኑ ተጠቁሟል።
በጤና ተቋማት ላይ ክፍተት መኖሩ እና በባህላዊ ህክምና ያለው የአሰራር ስህተት ዋነኞቹ ችግሮቾ መሆናቸውም ተነስቷል።
በጥናቱ ከ3 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የተካተቱ ሲሆን፥ በባህላዊ ወጌሻ የታከሙ፣ ወጌሻዎችን፣ የአጥንት ቀዶ ጥገናዎች፣ ምርምሮች፣ የፖሊሲ መሪዎች፣ በተለያዩ ተቋማት የሚሰሩ የጤና ተቋማት ይገኙበታል።
