ሩሲያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ ሂውማን ራይትስዎች የተባለውን የመብት ተሟጋች ድርጅት ሩሲያ “የማይፈለጉ ድርጅቶች”ብላ ከሰየመቻቸው ድርጅቶች ዝርዝር ውስጥ አካቷል።
የጀርመኑ የዜና ምንጭ ዲፒኤ እንደዘገበው፤ ርምጃውሂውማን ራይትስ ዎች በሩሲያ ውስጥ ያለውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ ወዲያውኑ እንዲያቆም የሚያደርግ እና በሩሲያ ውስጥ ያሉ ሰዎች ወይም ድርጅቶች ከድርጅቱ ጋር መስራትንም ሕገ-ወጥ ያደርጋል።
ሂዩማን ራይትስ ዎች ከሶስት አስርት አመታት በላይ ከድህረ-ሶቪየት ሩሲያ በኋላ ያለው መንግስት ሰብዓዊ መብቶችን እና ነጻነቶችን እንዲያስከብር ግፊት አድርጓል።
ሩሲያ ዋና ዋና ነጻ የዜና አውታሮችን እና የመብት ቡድኖችን ጨምሮ ከ270 በላይ ድርጅቶችን “የማይፈለጉ” ስትል ሰይማለች።
ሂውማን ራይትስ ወች የሩስያን ጦርነት አጥብቆ ሲተች የቆየ ሲሆን፤ የጦር ወንጀለኞች ናቸው ያላቸውን ዝርዝርም መዝግቧል።
በቅርቡ የሩስያ ወታደሮች ሰላማዊ ሰዎችን በሰው አልባ አውሮፕላኖች መግደላቸውን በምርመራ ይፋ አድርጓል።
