የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል የነበሩት ክቡር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሆነው ተሹመዋል።
ሹመቱን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባወጣው መግለጫ፣ ለአዲሱ ተሿሚ ስኬታማ የሥራ ጊዜ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ገልጿል።
አቶ ርስቱ ይርዳው ከዚህ ቀደም የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነውም አገልግለዋል።
