ማልሁልሽ ቃል ኪዳንም ገባሁልሽ አላት

Date:

የእግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን ለቅዱሳኑ ከሃይማኖታቸው ጽናት ከፍጹምነታቸውና ከሥራቸው ትሩፋት የተነሳ በቅድስና ክብር አክብሮ ለገድላቸው እንዲሁም በተጋድሎ ላሳለፉበት ቦታ ለረገጡት አፈር ሁሉ በረከታቸው ተርፎ ዛሬ እኛ ምእመናን በየመካናቱ እምነቱን በመተሻሸት በመጠጣት ከቅዱሳኑ በረከት እንሳተፋለንል፡፡

በዘጸአት 20÷2-6 እግዚአብሔር አምላክ ለሚወዱትም ትእዛዙን ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን እንደሚያደርግ ተጽፏል፡፡ በዘዳግም 7÷12 ደግሞ “እንዲህም ይሆናል፤ ይህችን ፍርድ ሰምተህ ብትጠብቃት ብታደርጋትም፥ አምላክህ እግዚአብሔር ለአባቶችህ የማለውን ቃል ኪዳንና ምሕረት ለአንተ ይጠብቅልሃል” ይላል፡፡ ኪዳነ ምህረት፣ የምህረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡

ይህም ፍጹም ከከበሩ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የማይጠፋ የዘላለም ኪዳን የሰጠበት ዕለት መታሰቢያ ነው፡፡ ታላቁ የነገረ ማርያም መጽሐፍ እንደሚያስረዳን ጌታችን ካረገ በኋላ እመቤታችን ጌታ ወደ ተቀበረበት ጎልጎታ እየሄደች ትጸልይ ነበር፡፡

በየካቲት 16 ቀንም ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ “ልጄ ወዳጄ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በቻለችህ ማኅፀኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለመሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ” እያለች ጸለየች፡፡ ጌታችንም መጥቶ ምን እንዲያደርግላት እንደምትፈልግ ጠየቀችው፡፡

ቅድስት ድንግል ማርያም በስሟ ለሚማጸኑ መታሰቢያዋን ለሚያደርጉ፣ ለችግረኛ ለሚራሩ፣ በስሟ ቤተ ክርስቲያን ለሚያንጹ፣ ዕጣን ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን ለሚሰጡ ምሕረትን እንዲያደርግላቸው ጠየቀችው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በአባቴ፣ በራሴና በመንፈስ ቅዱስ ማልሁልሽ ቃል ኪዳንም ገባሁልሽ አላት፡፡ ይህን የማያልፍ የምህረት ቃል ኪዳን ስለገባላትም ዕለቱ ኪዳነ ምሕረት የምሕረት የይቅርታ መሐላ፣ ውል፣ ስምምነት፣ ተብሎ በዝማሬ፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡

ምዕመናንም ዘወትር በረከትን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ይቀበላሉ፡፡ ገዳማውያንም ይህን ቃል ኪዳኗን አስበው ዘወትር ምህረትን አማልጂ ይሏታልና ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-
0918077957 ወይም 0938644444

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...