አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ የ10 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው

Date:



‎የሲዳማ ክልል ፍትሕ ቢሮ እንዳስታወቀው የቀድሞ የሲዳማ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች  ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ እና የቀድሞ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት ሽመልስ ቶማስ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ የእስራት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

‎የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀድሞው የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እና የፖሊስ ኮሚሽነር ላይ በክልሉ ፍትህ ቢሮ ከሳሽነት በቀረቡ ክሶች ላይ የጽኑ እስራት ውሳኔ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማመሳከር  ተከሳሾቹን ጥፋተኛ ያላቸው፤ ኃላፊዎቹ ስልጣንን አላግባብ በመገልገል የሲዳማ ነፃነት ሠራዊት (ሲነሠ) የተባለ ታጣቂ ቡድን በማደራጀትና ተደራራቢ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን በማረጋገጥ ውሳኔ ማስተላለፉን ቢሮው አስታውቋል።

‎በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 20/11/2018 ዓ.ም. በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሳሽ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴስ በ10 ዓመት ከ5 ወር ጹኑ እስራት እና 4000 ሺ ብር እንዲቀጡ እንዲሁም ሁለተኛ ተከሳሽ አቶ ሽመልስ ቶማስ በ1 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እና 1 ሺህ ብር እንዲቀጡ ውሳኔ ማስተላለፉን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአንጋፋውን ጋዜጠኛ ድምጽ እንደገና እንስማ

ኑ ጥቂት ድጋፍ አድርገን ተስፋ እናለምልም ‼️ ባለ ወርቃማ ድምጹ...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...