አዋሽ ኢንሹራንስ አጠቃላይ ገቢዉ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ሆነ

Date:

አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ. በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የገንዘብ አቅሙን በእጅጉ በማሳደግ፣ የተከፈለ ካፒታሉን በ38 በመቶ በማሳደግ ወደ 2.65 ቢሊዮን ብር ያደረሰ ሲሆን፣ አጠቃላይ የገቢ መጠኑም ከ4.53 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ይፋ አድርጓል።

አዋሽ ኢንሹራንስ የባለአክሲዮኖች 31ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እንደተገለጸው ፣ ኩባንያው በዓመቱ ከታክስ በፊት ብር 1 ቢሊዮን በላይ በማትረፍ በኢትዮጵያ የግል ኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የቢሊየን ብር ትርፍ አስመዝግቧል።

ኩባንያው በዋና ዋና የሥራ ዘርፎቹ ፈጣን ዕድገት ማስመዝገቡን የቀጠለ ሲሆን፣ በጀነራል ኢንሹራንስ የ43 በመቶ፣ በሕይወት ኢንሹራንስ የ48 በመቶ፣ እንዲሁም በተካፉል ዘርፍ ደግሞ የ124 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል።

ከጠቅላላው 4.53 ቢሊዮን ብር ገቢ ውስጥ በጄነራል ኢንሹራንስ ከ3.73 ቢሊዮን ብር በላይ፣ በሕይወት ኢንሹራንስ ከ656.27 ሚሊዮን ብር በላይ፣ እንዲሁም በተካፉል ዘርፍ ደግሞ ከ156 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን ለካፒታል በላከው መግለጫ ላይ አመልክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...