“አውሮፓውያን ትንንሽ አሳማዎች ናቸው” ፑቲን

Date:

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን  አውሮፓውያን ትንንሽ አሳማዎች ናቸው ሲሉ ወረፉ።

አውሮፓውያን ዩክሬንን  በመርዳት ጦርነቱ እንዳይቆም በማድረግ የሩሲያን ውድቀት የሚመኙ በማለት ፑቲን ተናግረዋል ።

አውሮፓውያን ከዚህ ቀደም በታሪክ ያጡትን ሁሉ  አሁን ሩሲያን በማዳከም ለማካካስ አሰፍስፈዋል ፣ ይህ ግን የሚያዛልቅ አይሆንም ነው ያሉት ፑቲን።

ሩሲያ ከአውሮፓ ጋር መደራደር ትፈልጋለች ፣ አሁን ያሉት ግን ያልበሰሉ ስለሆኑ አስቸጋሪ ናቸው ካሉ በኋላ የሩሲያ ጦር ምስጋና የሚገባዉ  ነው ብለዋል።

አሁን ላይ በዓለም  እንደሩሲያ ያለ ወታደራዊ አቅም ያለው፣ በጦር ሜዳ የተፈተነ ብሎም ልምድ ያለው ሰራዊት የለም ሲሉ ፑቲን ወታደሮቻቸውን አሞካሽተዋል።

ፑቲን ከጦር ሚኒስትሮቻቸው ጋር ዓመታዊ ስብሰባ ባደረጉበት ወቅት ነው አውሮፓውያንን ክፉኛ የወቀሱት።
  የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን መረን የለቀቀ  ድጋፍ በማድረጋቸው ተጠያቂ ናቸውም ብለዋል።

ፑቲን ለጦር ሚኒስትሮቻቸው የሰጡት ማብራሪያ እና መግለጫ ለተቀናቃኞቻቸው ጥብቅ መልዕክት ያዘለ እንደሆነ ያሳብቃል ይላሉ ተንታኞች ።

ፖለቲኮ ዘግቦታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...