የዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) የሥራ አመራር ቦርድ የኢትዮጵያን የ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ሦስተኛ ዙር የብድር ፕሮግራም አተገባበር ግምገማ ቀደም ሲል በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የድርጅቱ ቃል አቀባይ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የድርጅቱ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የግምገማ ሰነዱን ለማጽደቅ ቀጠሮ የያዘው፣ በቀጣዩ ሰኔ ወር ነው። ቦርዱ ግምገማውን ካጸደቀ፣ ድርጅቱ ከብድሩ 265 ሚሊዮን ዶላሩን ለአገሪቱ እንዲለቅ ያስችለዋል። የድርጅቱ የባለሙያዎች ቡድን በሚያዝያ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ገደማ ወደ ኢትዮጵያ አቅንተው ከባለሥልጣናት ጋር ተወያይተው እንደነበር ይታወሳል።
በግምገማው ዙሪያ መንግሥት ከባለሙያዎቹ ቡድን ጋር በጥቂት ቀናት ውስጥ ከስምምነት ላይ እንደሚደርስ የገንዘብ ሚንስትር ደኤታ እዮብ ተካልኝ በወቅቱ ተናግረው የነበረ ቢኾንም፣ እስካኹን ግን ስለ ስምምነት የተባለ ነገር የለም።
ዋዜማ
