ሴናተር ሊንድሲ ግርሃም ”ኢራን ኑክሌር ማበልፀጓን ከቀጠለችአሜሪካ ጥቃት መፈፀም ይኖርባታል ”አሉ።
ቴህራን በድጋሜ ወደ ኑክሌር ማብላላቱ መመለሷን የሚያረጋግጥ መረጃ ከተገኘ ዋሽንግተን ዳግም እርምጃ መዉሰድ አለባት ብለዋል።
በሌላ በኩል ኢራን ለሚሰነዘርብኝ ማናቸውም ጥቃት ሁሉ አፀፋዊ ምላሽ አለኝ ብላለች።
በቴል አቪቭ ለጋዜጠኞች ሀሳባቸውን ያጋሩት ሴናተሩ በሰኔው ጥቃት የቴህራን አቅም ተዳክሟል የሚል ሀሳባቸውንም አጋርተዋል።
የኢራን ሚሳዔሎች ግለፅ የእስራኤል ሰጋት መሆናቸውንም አልደበቁም ሴናተር ግርሃም::
አሜሪካን ‘ሰይጣን ‘አድርጋ የምትስለው ኢራን ካለፈው ስሀተቷ አልተማረችም በሚል ተችተዋል።
የቴህራን ፖለቲከኞችም አሜሪካና እስራኤል ጥቃት ለመሰንዘር ቢያሰቡም ምላሻችን ከሰኔው ጥቃት የከፋ ይሆናል በሚል ዝተዋል።
ኢራን ወደ ሙሉ የኑክሌር አቅም ከመምጣቷ በፊት መቅደም አለብን የሚል ሀሳብም ሰተዋል ሊንድሲ ግርሃም።
የ70 ዓመቱ የሳውዝ ካሮላይና ሴናተር በመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ላይ አስተያየት ሲሰጡ የአሁኑ የመጀመሪያቸው አይደለም።
ግርሃም የሪፐብሊካን ፓርቲ ዓባል መሆናቸውም ይታወቃል።
ዘገባው የአናዶሉ ነው።
