ኢትዮጵያን እድገት ለማረጋገጥ ለግብርና ትምህርት ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል

Date:

ኢትዮጵያን እድገት ለማረጋገጥ ለግብርና ትምህርት ትኩረት መስጠት ይገባል አሉ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር)፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ ኢትዮጵያ በርካታ የተፈጥሮ ሃብቶች፣ አምራች ዜጋ እና የቆየ ስራ ባህል እንዳላት አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብቷ ለግብርና ስራ ምቹ መሆኑን ጠቅሰው÷ ለአውሮፓ እና ለእስያ አህጉር የሚቀርብ የመሬት አቀማመጧ ለወጪ ንግድ ምቹ ሁኔታ መሆኑንም አብራርተዋል።

የሕዝብ ብዛት ተጨማሪ አቅም እና ሃብት በመሆኑ አምራች ኃይሉ አዳዲስ ዕውቀት እንዲቀስም በማድረግ ወደ ስራ ማስገባት ይቻላል ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ ግብርናን ጨምሮ በዘመናት ሂደት ያዳበረቻቸው ክህሎቶች አላት ያሉት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር)፤ ከራሷ አልፋ ሌሎችን እንድትረዳ የግብርና ትምህርት ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የአርሶ አደሩ ልጅ ከቤተሰቡ የግብርና እውቀት እንደሚያገኝ ጠቅሰው፤ ይህንን እውቀት በማዘመን የግብርና ምርታማነትን ማሳደግ ይቻላል ብለዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...