ኢትዮጲያ መድን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሻምፒዮን ሆነ

Date:

ተከታዩ ኢትዮጲያ ቡና ዛሬ ረፋድ ላይ ከመቀሌ 70 እንደርታ ጋር አቻ መለያየቱን ተከትሎ ኢትዮጲያ መድን ከተመሠረተ ከ42 አመታት በኅላ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሻምፒዮን መሆን ችሏል።

ኢትዮጲያ መድን በአሰልጣኝ ገብረ መድን ሀይሌ እየተመራ ማንም ሳይጠብቀዉ እና ሳያስበዉ በሊጉ ሶስት ጨዋታ እየቀረዉ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።

አንጋፋዉ አሰልጣኝ ገብረ መድን ሀይሌም ከሶስት የተለያዩ ክለቦች ጋር ሻምፒዮን በመሆን ለራሳቸዉ በኢትዮጲያ እግርኳስ ላይ አድስ ታሪክን ፅፈዋል።

ገብረ መድን ሀይሌ ከዚህ በፊት በ2010ከጂማ አባጂፋር ጋር እና በ2011 ከመቀሌ 70 እንደርታ ጋር የሊጉን ዋንጫ ከፍ ሲያረጉ አሁን ደግሞ ከኢትዮጲያ መድን ጋር ባለ ክብር ሆነዋል።

ኢትዮጲያ መድን ከዚህ በፊት በ1990 አመተ ምህረት ዋንጫዉን ለማንሳት ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም የኅላ ኅላ በኢትዮ ኤሌኬትሪክ በግብ ክፍያ ተበልጦ ዋንጫዉን ያጣ ሲሆን ገብረ መድን ሀይሌ ዘንድሮ ከናፈቀዉ የሊግ ዋንጫ ጋር አገናኝተዉታል።

የሊጉ መስራች ኢትዮጲያ መድን ሶስት ጊዜ ወርዶ እንደ ገና ሶስት ጊዜ ወደ ፕሪሚርሊግ አድጎ የሊጉን ዋንጫ ያነሳ የመጀመሪያዉ ቡድንም አድርጎታል።

ብስራት ኤፍ ኤም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተሰረቀ ዕቃ በቅናሽ ዋጋ መግዛት ወይም ይዞ መገኘት እስከ 3 ዓመት እስራት ያስቀጣል

በርካሽ ዋጋ የተሰረቁ ስልኮችን፣ ላፕቶፖችንና ሌሎች ዕቃዎችን መግዛት፣ የተሰረቀ...

በኢትዮጵያ በዓመት ከ18ሺህ በላይ ሴቶች በጡት ካንሰር ይጠቃሉ ተባለ

ጤና ሚኒስቴር  ከለሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር የጡት ካንሰር...

35ኛው ዓለም አቀፍ የስኳር ህመም ቀን ተከበረ

በዝግጅቱ ላይ የስኳር ህመምን ለመከላከል ቅድመ ምርመራን፣ ጤናማ አመጋገብንና...

በኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማእከል

መገናኛ ብዙሃን ሕጋዊ እና ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን በብቃት መወጣት እንዲችሉ...