የዓለም ደም ለጋሾች ቀን በመጪው ቅዳሜሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ኹነቶች እንደሚከበር የኢትዮጵያ ደምና ሕብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ለአራዳ ገልጿል።
ዕለቱን መነሻ በማድረግ ወሩን ሙሉ በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር ማቀዱንም አስታውቋል።
በዚህም የተለያዩ የንቅናቄና የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን በመስራትና የበጎፍቃድ የደም ማሰባሰብ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ እንደሚያከብር ነው የገለጸው።
መጪው የክረምት ወቅት በመሆኑና ትምህርት ቤቶችም ስለሚዘጉ የደም እጥረት እንዳይከሰት እየሰራሁ ነው ብሏል።
ዜጎች ደም በመለገስ ማህበራዊና ሰብዓዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስቧል።
@Arada_Fm
